ጉዳት እና ጥቃት ምን ማለት ነው?
ጉዳት ማለት አንድ ሰው ሲጎዳ እና ጉዳቱም ተጽእኖ ሲፈጥር ነው። ይህም በአካል መጎዳትን ብሎም የአንድን ሰው ስሜት ወይም የአእምሮ ደህንነት ጉዳትን ሊያካትት ይችላል።
ምንም እንኳን ብዙ ሰዎች ቅን ቢሆኑም ጥቃት የሚከሰተው አንዱ ሰው (ብዙውን ጊዜ አዋቂ) ሌላውን ሰው ሲጎዳ ነው፣ አብዛኛውን ጊዜ ሆን ተብሎ ወይም በግዴለሽነት ሊፈጸም ይችላል።
ምሳሌዎች…
ከጥቃት መጠበቅ ምን ማለት ነው?
ከጥቃት መጠበቅ ፥
1) እርስዎ ወይም ሌሎች እንዳይጎዱ ወይም እንዳጠቁ ይከለክላል።
2) አንድ ሰው ዳግምኛ አንዳይጎዳ ያግዳል ወይም እንዲያገግም ያግዘዋል።
3) በአጠቃላይ ሰዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ደስተኛ እና ጤናማ እንዲሆኑ ይደግፋል።
የሴፍ ፓሴጅ የደህንነት ጥበቃ አካሄድ ምን ይምስላል?
ሴፍ ፓሴጅ ውስጥ የሁሉም ድሀንነት የተጥበቀ መሆኑን አናረጋግጠልን። በተለይም ክሴፍ ፓሴጅ ጋር በሚስራ በማንም ሰው አንዳይጎዱ ወይም ሴፍ ፓሴጅ ከአርስዎ ጋር በመስራትዎ በየትኛውም ሁኒታ ጉዳት አንዳይድርስ የተቻለውን ሁሉ አናደርጋለን።
At Safe Passage, we have a responsibility to make sure you are not harmed and that you feel safe. This means Safe Passage representatives (staff, volunteers and partners) have rules to follow:
የሴፍ ፓሴጅ ወኪል የሆነ ሰው ምን ማድርግ ይጠብቅበታል
✅ ከእነሱ ጋር የሚገናኙትን ማንኛውንም ቦታ ደህንነቱ የተጠበቀ ለማድረግ ይሞክራል።
✅ አክብሮት እና እንክብካቤ ማሳየት።
✅ ማንኛውም አርስዎን ሚያሳስብ ወይም ጉዳት ላይ የጣለ ጉዳይ ካለና ልማውራት ፈቃደኘ ክሆኑ ብቻ ፣ እርስዎን ማዳመጥ እና ማነጋገር አለባቸው።
✅ እርስዎን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ውስጥ የሚቻል ከሆነ አንዲሳተፉ ያድርጋል።
✅ እርስዎን የሚመለከቱ መረጃዎችን በጥንቃቒ መያዝ።
የሴፍ ፓሴጅ ወኪል የሆነ ሰው በፍጹም ሊይድርግ የማይችላቸው
❌ በማንኛውም መልኩ መምታት ወይም አካልዎ ላይ ጉዳት ማድረስ።
❌ መጭህ፥ አርስዎን በሚያሰከፉ ስሞች መጥራት ወይም ስለራስህ መጥፎ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርግ ንግግሮችን መናገር።
❌ ማድረግ የማትፈልጋቸውን ነገሮች እንድታደርግ፣ ገንዘብ ወይም ሌላ ማንኛውንም ነገር መጠየቅ። ከሴፍ ፓሴጅ የሚያገኟቸው ሁሉም አገልግሎቶች ነጻ ናቸው።
❌ ያለ አግባብ የሆነ አካላዊ ንክኪ ወይም ጾታዊ ንግግር ማድረግ። ከእርስዎ ጋር ምንም አይነት የፍቅር ግንኙነት መፍጠር የለባቸውም።
❌ ቤትዎ መምጥት፣ ወይም ወደ ቤታቸው መጋበዝ።
❌ በማህበራዊ ሚዲያ (ኢንስታግራም፥ ፊስቡክ) ከእርስዎ ጋር መገናኘት ወይም ከእርስዎ ጋር ስላላቸው ስራ የማይገናኙ ነገሮችን መላክ።
በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ከሴፍ ፓሴጅ ተወካይ ጋር ብቻዎን አይሆኑም ፣ መሆንም ካለበት ህዝብ በሚሰብስብበት ቦታ ላይ ይሆናል።
የሴፍ ፓሴጅ ተወካይ ስህተት ከፈፀመ ምን አደርጋለሁ?
ማናቸውንም ደንቦች ከጣሱ ወይም እርስዎን ለመጉዳት ወይም የደህንነት ስሜት እንዳይሰማዎ የሚያደርግ ነገር ካደረጉ፣ በከሴፍ ፓሴጅ ውስጥ ላለ ሊላ ሰው መንገር አስፈላጊ ነው። ይህንንም ለማድረግ የተለያዩ መንገዶች አሉ እርስዎም የሚስማማዎትን በመምረጥ ማሳወቅ ይችላሉ።
ለ donoharm@safepassage.org.uk ኢሜል በማድረግ ምን እንደተፈጠረ ሊነግሩን ይችላሉ እንዲሁም በጉዳዩም የበለጠ ለመነጋገር መልሰን አንደውላለን/እንጽፍልዎታልን።
ከፊል ወይም ቤት ጋር መነጋግር ይችላሉ፥
ቤትን ወይም ፊልን ላያውቁ ይችላሉ፣ ወይም ከእነሱ ጋር ለመነጋገር ምቾት ባይሰማዎት፣ ሴፍ ፓሴጅ ውስጥ እርስዎ ለማነጋገር ከሚመችዎ ከሌላ ሰው ጋር መነጋገር ይችላሉ። ለምሳሌ የእርስዎ ጉዳይ ሰራተኛ(ኪዘ ወርከር) ወይም የበላይ አለቃቸው ሊሆን ይችላል።
ለማን እንደሚነግሩ ካላወቁ እዚህ ድረ-ገጻችን ላይም ሊነግሩን ይችላሉ። ይህ ቅጽ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛል። https://www.safepassage.org.uk/safeguarding-forms
ለሴፍ ፓሴጅ ሰራተኞች ሌላ ስለ ምን ልነግራቸው እችላለሁ?
እኛ እርስዎን ለመርዳት ዝግጁ ነን። በመሆኑም የሴፍ ፓሴጅ ተወካይ ስህተት ሲሰራ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጉዳይ ሊያነጋግሩን ይችላሉ። ጥሩ ስሜት ካልተሰማዎት ወይም ሌላ ሰው እየጎዳዎት ከሆነ ይህንንም ሊነግሩን ይችላሉ። ሁልጊዜ መፍትሄ ላይኖረን ይችላል፣ ነገር ግን ሁል ጊዜ ለመርዳት እንሞክራለን፣ ወይም ከሚችል ሰው ጋር እናገናኝዎታለን።
የሴፍ ፓሴጅ ሰራተኘ ለሆነ ሰው ስለአንድ ነገር ከነገርኩ በኋላ ምን ይከሰታል?
የሴፍ ፓሴጅ ተወካይ ስህተት እንደሰራ ከነገሩን ነገሩን እንመረምራለን። ምናልባትም አንድ ሰው ስለተፈጠረው ነገር እንደገና ሊያናግራችሁ ይችላል። ሌሎች ሰዎች እንዳይጎዱ ለማድረግም ለውጦችን ለማድረግ እንሞክራለን።
ሌላ ሰው እየጎዳዎት እንደሆነ ከነገሩን ከሌሎች ሰዎች ጋር መነጋገር ሊኖርብን ይችላል። በመጀመሪያ፣ ፊል ወይም ቤዝ በሴፍ ፓሴጅ ሁልጊዜ ሊነገራቸው ይገባል፣ ነገር ግን ከሴፍ ፓሴጅ ውጪ ላሉ ሰዎች ጭምርም መንገር ሊኖርባቸውም ይችላል። ምናልባትም የእርስዎን ደህንነት ለመጠበቅ የሚረዳ የማህበራዊ ሰራተኛ ወይም ሌላ ሰው ሊሆንም ይችላል። እርስዎን ሊጎዳ ወይም ሁኔታውን ሊያባብስ ለሚችል ሰው በጭራሽ መረጃ አናጋራም።
የተናገርኩት ነገር በሚስጥር ይያዛል?
ምስጢር አይደለም። አንድ ሰው የተጎዳ ወይም ጥቃት የደረሰበት ከሆነ ይህን በሚስጥር ልንይዘው አንችልም። ሆኖም በጣም በጥንቃቂ ለማን እንደሚነገር እና ማወቅ ለሚያስፈልጋቸው ብቻ እንነግራቸዋለን። ይህ የሚያስፈራ ሊመስል ይችላል እናም በሚስጥር ልታስቀምጠው ትፈልግ ይሆናል፣ነገር ግን እኛ ለመሞከር እና ለመርዳት እንድንችል እንደምትነግረ/ሪን ተስፋ እናደርጋለን
ስለ ደህንነት ጥበቃ ሊላ ማንኛውም ጥያቂ ኣለዎት?
እንዴት የተሻለ መስራት እንደምንችል ሀሳብ አሎት?
ከሆነ እባክዎን ፊልን ያነጋግሩ ወይም donoharm@safepassage.org.uk ኢሜይል ያድርጉ
ስምዎን ማሳወቅ ሳይያስፈልግዎት ስም-ኣልባ ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ። ነገር ግን ስም-አልባ ሪፖርት ካደረጉ ሁኒታውን ባግባቡ የመመርመር እና ምላሽ የመስጠት ኣቅማችንን ላይ ከፍተኛ ተጽአኖ ሊያድርግ ይችላል።